ፈሳሽ ትራፊዎች (ኣሳር)

4350

      የትራፊዎች (ኣሳር) ትርጓሜ

ፈሳሽ ትራፊዎች

ሌላ ጠጪ ጠጥቶለት እቃ ውስጥ ያስቀረው ትራፊ ጭላጭ ነው፡፡

    ለነጃሳነቱ ማስረጃ ካልቀረበበት በስተቀር ፈሳሽ ትራፊዎች (ኣሳር) በመሰረቱ ንጹሕ (ጣህር) ናቸው፡፡ ዝርዝሩ ይቀጥላል፡-

    ንጹሕ የሆኑ ትራፊዎች

    ሀ- የሰው ልጅ ጠጥቶ ያስቀረው ትራፊ

    ነቢዩ ﷺ፣ዓእሻ (ረዐ) የወር አበባ እያለባቸው ጠጥተው ያስቀሩትን ትራፊ ይጠጡ እንደ ነበርና አፋቸውንም የዓእሻ አፍ አርፎ በነበረበት ቦታ ላይ ያደርጉ እንደ ነበር [በሙስሊም የተዘገበ] በሐዲስ ተረጋግጧል፡፡

    ለ - የድመት ትራፊ (ሱእር)

    ከእቃ የጠጣችውን ድመት አስመልክተው ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ነጃሳ አይደለችም፣በዙሪያችሁ ከሚሆኑ ገርና ጥንቁቅ አገልጋዮች ናት፡፡›› [በትርምዚ የተዘገበ]ብለዋል፡፡

    የድመት ትራፊ

    ሐ- ሥጋቸው የሚበላ እንስሳት፣የበቅሎ፣የአህያ፣ሥጋ በል አዳኝ አራዊት፣አዳኝ አሞራዎችና የመሳሰሉት እንስሳት ትራፊ፡-

    የነዚህ እንስሳት ትራፊ ንጹሕ ነው፡፡ ነጃሳ ስለመሆናቸው ማስረጃ ባለመኖሩና ነገሮች ተቃራኒው ካልተረጋገጠ በመሰረቱ ንጹሕ በመሆናቸው የነዚህ እንስሳት ትራፊ ንጹሕ ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ በአህያ ይቀመጡ ነበር፡፡ በዘመናቸው አህያ ለማጓጓዣነት ታገለግል ነበር፡፡

    የአዳኝ አሞራ (አዕዋፍ) ትራፊ
    የአህያ ትራፊ
    የአዳኝ አውሬ ትራፊ
    ሥጋው የሚበላ እንስሳ ትራፊ ውሃ

    ነጃሳ የሆኑ ትራፊዎች

    ሀ - የውሻ ትራፊ

    ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ያንዳችሁን ዕቃ ውሻ በአፉ (ምላሱን በማስገባት) ከለከፈው የሚጸዳው (ዕቃውን) ሰባት ጊዜ አንደኛውን ዙር በአፈር በማጠብ ነው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]

    የውሻ ትራፊ

    ሀ - የአሳማ ትራፊ

    የአሳማ ትራፊ (ሱእር) ነጃሳ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እርሱ ርኩስ ነውና . . . ›› [አል-አንዓም፡145]፡፡ ከርሱ የወጣ ነገርም ነጃሳ ነው፡፡

    የአሳማ ትራፊ
    የሰው ልጅ ንጹሕ (ጣህር) መሆኑ
    የሰው ልጅ፣ነቢዩ ﷺ፡- ‹‹ሙእምን ሰው አይነጅስም፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ባሉት መሰረት ሙስሊም በራሱ ንጹሕ (ጣህር) ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ ሙሽሪክ ከሆነች ሴት የውሃ ስልቻ ዉዱእ ማድረጋቸው የተረጋገጠ [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] በመሆኑ ሆነ ካፍርም በራሱ ንጹሕ (ጣህር) ነው፡፡ ‹‹አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፤›› [አል-ተውባህ፡28] የሚለው የአላህ U ቃል ሕሊናዊ ርክሰት ማለትም የእምነታቸውን ነጃሳነት የሚመለከት ነው፡፡