ሶላትን የሚመሰርቱ፣ለማድረግ ያለመቻል ሁኔታ ብቻ ሲቀር በምንም ሁኔታ ሊተው የማይችሉ፣በማወቅም ሆነ በመዘንጋት ውድቅ የማይሆኑ የሶላት መሰረታዊ ክፍሎች ናቸው፡፡
ሶላትን የሚመሰርቱ፣ለማድረግ ያለመቻል ሁኔታ ብቻ ሲቀር በምንም ሁኔታ ሊተው የማይችሉ፣በማወቅም ሆነ በመዘንጋት ውድቅ የማይሆኑ የሶላት መሰረታዊ ክፍሎች ናቸው፡፡
1 - ንይ’ያህ ማድረግ፡፡
2 - በግዴታ ሶላት አቅም እስካለ ድረስ መቆም፡፡
3 - የእሕራም ተክቢራ፡፡
4 - ፋቲሓን መቅራት፡፡
5 - ሩኩዕ፡፡
6 - ከሩኩዕ ቀና ብሎ መቆም (እዕትዳል)፡፡
7 - በሰባቱ አካላት ሱጁድ መውረድ፡፡
8 - በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ፡፡
9 - ለመጨረሻው ተሸሁድ መቀመጥ፡፡
10 - የመጨረሻውን ተሸሁድ መቅራት፡፡
11 - በመጨረሻው ተሸሁድ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶላት ማውረድ፡፡
12 - ሰላምታ (ተስሊም)፡፡
13 - በሁሉም ማእዘናት ውስጥ የእርጋታ (ጡመእኒና) መኖር፡፡
14 - የማእዘናቱን ቅደም ተከተል መጠበቅ፡፡
ሀ- ማእዘኑን የተወ መሆኑን እስከ ቀጣዩ ረክዓ ተመሳሳይ ማእዘን ቦታ ድረስ አለማስታወስ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሩክኑን የተወበት ይህ ረክዓ አይቆጠርም፡፡ ቀጣዩን ረክዓ የተሳሳተበት ረክዓ አድርጎ በመጨረሻ ላይ የመሳሳት ሱጁድ ያደርጋል፡፡
ምሣሌ፡- አንድ ሰጋጅ በሁለተኛው ረክዓ ፋቲሓ መቅራት ሲጀመር በመጀመሪያው ረክዓ ረስቶ ፋቲሓ ያልቀራ መሆኑን ያስታውሳል፡፡ ስለዚህም ፋቲሓ ያልተቀራበትን ረክዓ ሰርዞ ሁለተኛውን ረክዓ የመጀመሪያው ረክዓ ያደርጋል ማለት ነው፡፡
ለ- ወደ ሁለተኛ ረክዓ ቦታው ከመድረሱ በፊት አንዱን ማእዘን መርሳቱን የሚያስታውስበት ሁኔታ፡፡ በዚህ ሁኔታ እንዳስታወሰ ወዲያውኑ ተመልሶ ማእዘኑን ማከናወን ይኖርበታል፡፡
ምሣሌ፡- ቅራአውን ካበቃ በኋላ ሩኩዕን ረስቶ ሱጁድ የወረደና ሱጁድ ላይ ሆኖ ሩኩዕ መርሳቱን ያስታወሰ ሰው ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ተነስቶ በመቆም ሩኩዕ ያደርግና ሶላቱን ይቀጥላል፡፡
በመርሳት ሱጁድ የሚካካስና ከተረሳ የሚቀር፡፡
1 - በሶላት ክፍሎች መካከል የሚደረጉ የመሸጋገሪያ ተክቢራዎች፡፡
2 - ሩኩዕ ላይ ‹‹ሱብሓነ ረብ’ቢየል ዐዚም›› ማለት፡፡
3 - ‹‹ሰምዐል’ሏሁ ልመንሐምደህ›› ማለት፡፡ ለኢማምና ለብቻው ለሚሰግድ ሰው፡፡ ለመእሙም የተደነገገ አይደለም፡፡
4 - ከሩኩዕ ቀና ሲባል ‹‹ረብ’በና ወለከል ሐምዱ›› ማለት፡፡
5 - ሱጁድ ውስጥ ‹‹ሱብሓነ ረብ’ቢየል አዕላ›› ማለት፡፡
6 - በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ‹‹ረብብ እግፍርሊ›› ማለት፡፡
7 - ለመጀመሪያው ተሸሁድ መቀመጥ፡፡
8 -የመጀመሪያው ተሸሁድ፡፡
1 - ሆን ብሎ የተወ ሰው ሶላቱ ስለሚበላሽ መድገም ግዴታ ይሆንበታል፡፡
2 - ረስቶት የተወው ሰው ሶላቱ ትክክለኛ ሲሆን፣በመጨረሻ ሁለት የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡
ከሶላት ሸርጥ፣ከማእዘናቱና ከግዴታዎቹ ውጭ ያሉና በሶላት አሰጋገድ ውስጥ የተጠቀሱ ነገሮች ሁሉ የሶላት ሱንናዎች ናቸው፡፡ ቢተው በሶላቱ ትክክለኛነት ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ የለም፡፡ በመተውም የማካካሻ ሱጁድ ማድረግ ግዴታ አይሆንም፡፡
የሶላት ሱንናዎች ሁለት ዓይነት ሲሆኑ በቁጥርም ብዙ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል የሚከተሉትን እናገኛለን ፡-
1 - የመክፈቻው ዱዓእ ፡- ይህ ከፋቲሓ በፊት የሚቀራው ዱዓእ ነው፡፡
2 - ተዐው’ዉዝ ፡- ‹‹አዑዙ ብል’ላሂ ምነሽ’ሸይጣንር’ረጂም›› ማለት፡፡
3 - በስመላህ ፡- ‹‹ብስምል’ላህር’ረሕማንር’ረሒም›› ማለት፡፡
4 - በሩኩዕና በሱጁድ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ ተስቢሕ ማለት፡፡
5 - በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ከአንድ ጊዜ በላይ ‹‹ረብ’ብ እግፍርሊ›› ማለት፡፡
6- ከሩኩዕ ቀና ካሉ በኋላ ‹‹ረብ’በና ወለከል ሐምዱ›› በሚለው ላይ የሚጨመር ዝክር፡፡
7 - ከፋቲሓ በኋላ የሚቀራ ተጨማሪ ቁርኣን፡፡
ተግባራዊ ሱንናዎች ብዙ ሲሆኑ የሚከተሉት ከፊሎቹ ናቸው ፡-
1 - ከእሕራም ተክቢራ ጋር፣ሩኩዕ ሲወርዱ፣ከሩኩዕ ቀና ሲሉ፣ለሦስተኛ ረክዓ ለመቆም ሲነሱ ሁለት እጆችን ከፍ ማድረግ፡፡
2 - ከሩኩዕ በፊትና በኋላም በሚቆሙበት ጊዜ ቀኝ እጅን በግራው ላይ ማድረግ፡፡
3 - የሱጁድ ቦታን መመልከት፡፡
4 - በሱጁድ ላይ ሁለት እጆችን ከሆድና ከጎድን ማራራቅ፡፡
5 - እፍትራሽ ማለትም ግራው ላይ ተቀምጦ ጣቶቹን ወደ ቅብላ በማድረግ ቀኙን ተረከዝ ማቆም፡፡ ይህ አቀማመጥ ከሁለት ረክዓ በሚበልጡ ሶላቶች የመጨረሻው ተሸሁድ ብቻ ሲቀር በሁሉም ሶላቶች ውስጥ ሱንና ነው፡፡
6 - ተወርሩክ ማለትም መቀመጫን ከመሬት አድርሶ በመቀመጥ የግራ እግርን በቀኝ በኩል አውጥቶ መሬት ላይ በማስተኛት ቀኝ ተረከዝን ማቆም፡፡ ይህ አቀማመጥ ከሁለት ረክዓ ለሚበልጡ ሶላቶች በመጨረሻው ተሸሁድ ሱንና ነው፡፡