የመገልገያ እቃዎች

3729

      የእቃዎች (ኣኒያ) ትርጓሜ

የመገልገያ እቃዎች

የውሃና የሌሎች ነገሮች መያዣ እቃዎች

    የወርቅና የብር እቃዎችን ስለ መጠቀም

    1 - በምግብና በመጠጥ

    ለመመገቢያነትና ለመጠጫነት መጠቀም የተከለከለ ሐራም ነው፡፡ ይህም ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹በወርቅና ብር እቃዎች አትጠጡ፡፡ በሳፋዎቻቸውም አትብሉ፤ በዚች ዓለም ላይ የነሱ (የካፍሮች) በመጨረሻይቱ ዓለም የኛ ናቸው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]

    ባሉት መሰረት ነው፡፡ በተጨማሪም፡- ‹‹በብር እቃ ሚጠጣ ሰው የጀሀነምን እሳት እንጂ ሌላ አይደለም ወደ ሆዱ የሚያዶቀድቀው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]

    በብር እቃ መመገብ
    በወርቅ እቃ መመገብ

    2 - ከምግብና ከመጠጥ ውጭ

    ከምግብና ከመጠጥ ውጭ በዉዱእና በሌላም የወርቅና የብርና እቃዎችን መጠቀም ይፈቀዳል፤ከላይ የቀረበው ሐዲሥ በምግብና በመጠጥ ብቻ የተወሰነ ነውና፡፡ በተጨማሪም ኡምሙ ሰለማ (ረዐ) ከነቢዩ ﷺ ጸጉሮች ጥቂት ጸጉሮች ያሉበት ከብር የተሰራ ደወል መሰል ትንሽ እቃ እንደነበራቸው ተረጋግጧል፡፡ [በቡኻሪ የተዘገበ]

    ከብር የተሰራ የወዱእ ማድረጊያ እቃ (እብሪቅ)

    በብር በተበየደ እቃ መገልገል

    መጠኑ አነስተኛ በሆነ ብር የተበየደ እቃን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ መጠቀም ይፈቀዳል፡፡ የነቢዩ ﷺ የመጠጫ ዋንጫ ተሰብሮ በስንጥቁ ቦታ የብር ሰንሰለት መደረጉ [በቡኻሪ የተዘገበ] ተረጋግጧል፡

    በብር በተበየደ እቃ መገልገል
    ወርቅ ለወንዶች አይደለም
    ለወንድ ወርቅ መልበስ (ማድረግ) አይፈቀድም፡፡ ከአቡ ሙሳ አል አሽዐሪ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት የአላህ መልእክተኛ ﷺ ፡- ‹‹ሐርና ወርቅን መልበስ በኔ ኡመት ወንዶች ላይ ሐራም ተደርጎ ለሴቶቻቸው ተፈቅዷል፡፡›› [በትርምዚ የተዘገበ] ብለዋል፡፡