በመጸዳዳት ጊዜ መደረግ ያለባቸው ነገሮች
1 - በመጸዳዳት ጊዜ ሀፍረተ ገላን
(ዐውረትን) ከሰዎች እይታ መሰወርና መሸፈን፤ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹በጅኖች ዓይኖችና በኣደም ልጆች ሀፍረተ ገላ መካከል ያለው መጋረጃ ወደ መጸዳጃ ቦታ ሲገባ ‹ብስምል’ላህ› ማለት ነው፡፡ ›› [በትርምዚ የተዘገበ]ብለዋል፡፡
2 - ልብስ ወይም ገላ በነጃሳ እንዳይነካ መጠንቀቅና ከነካ ማጠብ፤የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሁለት መቃብሮች አጠገብ ሲያልፉ ፡- ‹‹እየተሰቃዩ ነው፤የሚሰቃዩትም በትልቅ ነገር (ጥፋት) ምክንያት ሳይሆን ይኸኛው ራሱን ከሽንት አይጠብቅም፣አይጠነቀቅም ኖሯል፡፡›› [በአቡ ዳውድ የተዘገበ]ብለዋል፡፡
3 - በውሃ ወይም በደረቅ ነገር መጸዳዳት (እስትንጃእ ወይም እስትጅማር)፤ከአነስ ብን ማሊክ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት የአላህ መልእክተኛ ﷺወደ መጸዳጃ ቦታ ሲሄዱ እኔና ሌላው ብላቴና (ልጅ) የውሃ መያዣውንና አንካሴ ይዘንላቸው እንሄድና በውሃ ይታጠቡ (እስትንጃእ ያደርጉ) ነበር፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ብሏል፡፡
በመጸዳዳት ጊዜ የተከለከሉ (ሐራም የሆኑ) ነገሮች
1 - ምድረበዳ ላይ በመጸዳዳት ጊዜ ፊትን ወደ ቅብላ ማዞር ወይም ጀርባን አለመስጠት፤ለመጸዳጃነት በተዘጋጀ የተለየ ግንባታ ከሆነ፣ ፊትን ወደ ቅብላ ማዞርንም ሆነ ለቅብላ ጀርባ መስጠትን መተው ተመራጭ ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹በመጸዳዳት ጊዜ በውሃ ሽንትም ሆነ በዓይነ ምድር ፊታችሁን ወደ ቅብላ አታዙሩ፡፡ ጀርባችሁንም አትስጡት፤ወደ ምሥራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]ብለዋል፡፡
2 - በመንገዶች ላይ፣ሰዎች በሚጠለሉበት ጥላ ቦታና በመሰብሰቢያ ቦታዎች መጸዳዳት፤ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ሁለቱን መርገምት ተጠንቀቁ ሲሉ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሁለቱ መርገምት ምንድነው? ተብለው ሲጠየቁ በሰው መንገድ ወይም በሚያርፉበት ጥላ ቦታ የሚጸዳዳ ሰው ነው፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]ብለዋል፡፡
3 - ወራጅ ባልሆነ እንደ ገላ መታጠቢያ ገንዳ ባለ ውሃ ውስጥ መረዳዳት፤ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹አንዳችሁ በማይፈስ የረጋ ውሃ [የረጋ ውሃ የማይወረድና የማይንቀሳቀስ ውሃ ነው] ላይ ይሸናና እዚያው ደግሞ ይታጠባልን? (አታድርጉ)፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]ብለዋል፡፡
4 - የቁርኣን መጽሐፍ ይዞ መጸዳጃ ቤት መግባት ሐራም ነው፡፡
በገላጣ ቦታ ላይ መጸዳዳት
ሰው በሚጓዝበት መንገድ ላይ መጸዳዳት
በመጸዳዳት ጊዜ የሚወደዱ (ሙስተሐብ) ነገሮች
1 - ምድረበዳ ላይ በሚጸዳዱበት ጊዜ ከሰው እይታ ርቆ መሄድ፡፡
2 - ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገባ ፡- ‹‹ብስምል’ላህ፣ አል’ሏሁም’መ እን’ኒ አዑዙ ብከ ምነልኹብሥ ወልኸባእሥ›› ትርጉሙ፡- ‹‹በአላህ ስም፣ አላህ ሆይ ከተባእትና አነስት ሰይጣናት (ተንኮል) በአንተ እጠበቃለሁ፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ማለት ነው፡፡
3 - ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገባ የግራ እግርን ማስቀደም ሲወጣ ደግሞ ቀኑን ማስቀደም፡፡
4 - በሚወጡበት ጊዜ ‹‹ጉፍራነከ›› [በአቡ ዳውድ የተዘገበ] (ምሕረትህን ስጠኝ) ማለት፡፡
ሲወጡ ቀኝ እግርን ማስቀደም
ሲገቡ ግራ እግርን ማስቀደም
በረጋ ውሃ ላይ መሽናት
በረጋ ውሃ ውስጥ መሽናት በደም መጣጭ ጥገኛ ትሎች የሚመጣውን የብልሃርዚያ በሽታ ያስከትላል፡፡
በመጸዳዳት ጊዜ የተጠሉ (መክሩህ) ነገሮች
1 - ሲጸዳዱ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ መናገር ወይም ሌሎችን ማናገር፤ይህም ከእብን ዑመር (ረዐ) በተላለፈውና ነቢዩ ﷺ በመጸዳዳት ላይ እያሉ በአቅራቢያቸው ያለፈ አንድ ሰው ሰላምታ ሲያቀርብላቸው ሰላምታውን አልመለሱለትም፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]በሚለው ሐዲሥ መሰረት ነው፡፡
2 - ይሰረቅብኛል ወይም ይጠፋል የሚል ስጋት ከሌለ የአላህ U ስም ያለበትን ነገር ይዞ መግባት፡፡
3 - ብልትን በቀኝ እጅ መንካት ወይም በቀኝ እጅ እስትንጃእም ሆነ እስትጅማር ማድረግ፤ ነቢዩ ﷺ ‹‹አንዳችሁ ሲሸና ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዝ፤ከዓይነ ምድር ሲጸዳዳም በቀኝ እጁ አያድርግ፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]
4 - ተሳቢ እንስሳት እንዳይጎዱት ወይም እንዳይጎዳቸው ሲባል በስጥቆችና ጉድጓዶች መሽናት፡፡
አላህን የሚያወሳ ነገር ያለበትን ነገር ይዞ መጸዳጃ ቤት መግባት
እየተጸዳዱ መናገር
በአውሬ ጉድጓድ ቦታዎች መሽናት
የቁርኣን መጽሐፍ ይዞ መጸዳጃ ቤት መግባት
ቆሞ መሽናት
ነቢዩ ﷺ ቆሞ መሽናትን ከልክሏል፡፡ ይሁን እንጂ ሽንቱ የማይረጭበት መሆኑን ካረጋገጠ ይፈቀዳል፡፡ ከሑዘይፋ (ረዐ) ‹‹የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሰዎች ቆሻሻ በሚጥሉበት ስፍራ ሄደው ቆመው ተጸዳዱ፡፡›› [በቡኻሪና በሙስሊም የተዘገበ]የሚል ሐዲስ ተዘግቧል፡፡
እስትንጃእና እስትጅማር