ጥቅም ሊሰጥ የሚችል ከመሬት የሚወጣ ማንኛውም ነገር ነው፡፡
ጥቅም ሊሰጥ የሚችል ከመሬት የሚወጣ ማንኛውም ነገር ነው፡፡
tከመሬት የሚወጣው ሁለት ዓይነት ሲሆን እህልና ፍራፍሬ፣ ማዕድንና የተቀበሩ ንብረቶች ናቸው፡፡
እንደ ገብስና ስንዴ ያሉ ለቀለብ የሚቀመጡ የእህል ዓይነቶች ሁሉ ናቸው፡፡
እንደ ተምር ዘቢብና ለውዝ ያሉ ለቀለብ መቀመጥ የሚችሉ ፍራፍሬዎች ሁሉ ናቸው፡፡
የእህልና ፍራፍሬ ዘካትን መክፈል ዋጅብ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏልና ፡- ‹‹በአጨዳው ቀን፣ተገቢውን (ዘካት) ስጡ፤›› [አል-አንዓም፡141]
ነቢዩም ﷺ ‹‹በዝናም ወይም በተጠራቀመ የተፈጥሮ ውሃ (የተመረተ) ከሆነ አንድ አስረኛወን፣በጉድጓድ ውሃ (የተመረተ) ከሆነ የአንድ አስረኛ ግማሽ (አምስት ከመቶ የዘካት ክፍያ) ይከፈላል፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] ብለዋል፡፡
የሚቆይና የሚቀመጥ ሳይሆን ለዕለታዊ ፍጆታ ብቻ የሚውል ከሆነ፣በዚህ ሁኔታ ወደ ገንዘብነት የማይለወጥና የተሟላ የንብረትነት ጥቅም የማይሰጥ በመሆኑ ዘካት አይከፈልበትም፡፡
በአውሱቅ (የመስፈሪያ ዓይነት ነው) የሚሰፈር መሆን፡፡ ‹‹በእህልም ሆነ በተምር አምስት አውሱቅ [አንድ ወሰቅ ስልሳ ሷዕ ነው] እስኪደርስ ድረስ ሰደቃ (የዘካት ክፍያ) የለበትም፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ] የሚለው የነቢዩﷺ ቃል የዚህን ሸርጥ አስፈላጊነት ያረጋገጣል፡፡
እንደ አትክልትና በቆልት ያለ የማይሰፈር ከሆነ ዘካት አይከፈልበትም፡፡
በገዛ ራሱ የበቀለው ወፍ ዘራሽ ግን ዘካት አይከፈልበትም፡
ይህም አምስት አውሱቅ ነው፡፡ ነቢዩﷺ ‹‹በእህልም ሆነ በተምር አምስት አውሱቅ እስኪደርስ ድረስ ሰደቃ (የዘካት ክፍያ) የለበትም፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ] ብለዋልና፡፡
የዘካት መክፈያው አነስተኛ መጠን (ንሷብ) ሦስት መቶ ነቢያዊ ሷዕ ሲሆን፣ ይህም 612ኪሎ ግራም ጥሩ ዓይነት ገብስ ነው፡፡ ንሷቡን ለመሙላት ያንድ አዝመራ ወቅት ተመሳሳይ እህል፣ለምሳሌ አንዱ የተምር ዓይነት ከሌላው የተምር ዓይነት ጋር ይደባለቃል፡፡ ንሷቡን ለመሙላት አንዱ የእህል ዓይነት ዝርያው ካልሆነ የእህል ዓይነት ጋር፣ለምሳሌ አጃ ከገብስ ጋር ወይም ከተምር ጋር አይቀላቀልም፡፡
የእህል ሰብል ዘካ መክፈያ ጊዜ ፍሬው ሲጠነክር ሲሆን የፍራፍሬውም ፍሬው ሲበስልና ለመብላት ምቹ በሚሆንበት ጊዜ ነው፡፡ እህሉን ወይም ፍራፍሬውን ከደረሰና ከጎመራ በኋላ የሸጠ ሰው የዘካት ክፍያውን የሚሸከመው ሻጩ ነው፡፡ ዘካው ግዴታ ሲሆን ባለቤት የነበረው እሱ ነውና፡፡
1 -የዝናምና የምንጭ ውሃን በመሳሰለ ውሃ በመጠቀም ያለ መሳሪያና ያለ ወጭ ከተዘራው ላይ አንድ አስረኛ (10%) ይከፈልበታል፡፡
2 - እንደ ጉድጓድ ውሃ ባለ ጥረትና ወጭን በሚጠይቅ ውሃ በተዘራው ላይ ግን የአንድ አስረኛ ግማሽ (5%) ይከፈልበታል፡፡
3 - አንዳንዴ በዝናም ውሃ አንዳንዴ ደግሞ በጉድጓድ ውሃ በመጠቀም በሁለቱ ጥምረት በተዘራው የአንድ አስረኛ ሦስት አራተኛ (7.5%) ይከፈልበታል፡፡ ለዚህ ማሰረጃው ነቢዩﷺ ‹‹በዝናም፣በወንዞችና በምንጮች ውሃ በተዘራው አንድ አስረኛ፣በግመል ጉልበት በሚወጣ የጉድጓድ ውሃ (የተመረተ) ከሆነ የአንድ አስረኛ ግማሽ ይከፈላል፡፡››[በቡኻሪ የተዘገበ] ማለታቸው ነው፡፡
እንደ ወርቅ፣ብር፣ብረት፣ዕንቁዎችና እርሳስ ያሉ ከመሬት የሚወጡ ጥሬ ሀብቶች ናቸው፡፡
መሬት ውስጥ በሰው እጅ የተቀበረ ወርቅና ብርን የመሳሰለ ሀብት ነው፡፡
ዘካው ዋጅብ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏልና ፡- ‹‹እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ካፈራችሁትና ከዚያም ለናንተ ከምድር ካወጣንላችሁ ከመልካሙ ለግሱ፤›› [አል-በቀራህ፡267]
ነቢዩም ﷺ ‹‹ተቀብረው በሚገኙ ንብረቶች (የዘካት ክፍያ መጠን) አንድ አምስተኛ ነው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ብለዋል፡፡
ተቀብሮ የተገኘ ገንዘብ ምንም ቅድመ ሁኔታ የለውም፣አንድ ሰው ንብረቱን ካወጣ ዘካውን ወዲያውኑ ይከፍላል፡፡
ለብዙም ሆነ ለአነስተኛ መጠን የዘካት ክፍያ መጠኑ አንድ አምስተኛ ነው፡፡ ይህም ‹‹ተቀብረው በሚገኙ ንብረቶች (የዘካት ክፍያ መጠን) አንድ አምስተኛ ነው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] በሚለው የነቢዩﷺ ሐዲስ መሰረት ነው፡፡