የዑምራ ማእዘናት ዋጅቦችና ሱናዎች

2842

    የዑምራ ማእዘናት

    1 - እሕራም፡፡

    ነቢዩﷺ ‹‹ሥራዎች (የሚለኩት ከጀርባቸው ባለው ቁርጠኛ) ውሳኔ ነው፤እያንዳንዱ ሰውም በንይ’ያው መሰረት ነው የሚያገኘው፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] ብለዋልና፡፡

    2 - በሶፋና መርዋ መካከል መመላለስ (ሰዕይ)፡፡

    ነቢዩ ﷺ ‹‹ተመላለሱ፤አላህ መመላለስን (ሰዕይን) ግዴታ አድርጎባችኋልና፡፡›› [በአሕመድ የተዘገበ] ብለዋል፡፡

    3 - ጠዋፍ ማድረግ፡፡

    አላህ እንዲህ ብሏልና ፡- ‹‹በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ፡፡›› [አል-ሐጅ:29]

    እሕራም

    የዑምራ ዋጅቦች

    1 - ከሚቃት እሕራም ማድረግ፡፡

    ነቢዩﷺ ሚቃቶችን ከጠቀሱ በኋላ ‹‹እነዚህ ለነሱና የነዚያ ነዋሪዎች ሳይሆኑ በነሱ በኩል ሐጅና ዑምራ ፈልገው ለሚመጡትም ናቸው፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] ብለዋልና፡፡

    2 - ጸጉር መላጨት ወይም ማሳጠር፡፡

    አላህ ፡- ‹‹አላህ የሻ እንደ ኾነ ጸጥተኞች ኾናችሁ፣ራሶቻችሁን ላጭታችሁ፣አሳጥራችሁም የማትፈሩ ስትኾኑ፣የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ፤›› [አል-ፈትሕ:27] ብሏልና፡፡

    የዑምራ ሱናዎች

    ከማእዘናትና ከዋጅቦች ውጭ ያሉት ሁሉ ሱንናዎቹ ሲሆኑ እነሱም የሚከተሉት ናቸው ፡-

    - ማሳሰቢያ...

    1 - ከዑምራ ማእዘኖች ውስጥ አንዱን የተወ ሰው እስኪያሟላው ድረስ ዕባዳው የተሟላ መሆን አይችልም፡፡

    2 - ከዑምራ ዋጅቦች ውስጥ አንዱን ዋጅብ የተወ ሰው የእርድ ግዴታ (አንድ ፍየል፣የበሬ ወይም የግመል አንድ ሰባተኛ) አለበት፡፡

    3 - ከዑምራ ሱናዎች አንዱን የተወ ሰው ምንም የለበትም፣ዑምራውም ትክክለኛ ነው፡፡

    እሕራም
    ጸጉር መላጨትና ማሳጠር
    ገላን መታጠብ