ዓይነምድርን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች

4495

      በመጸዳዳት ጊዜ መደረግ ያለባቸው ነገሮች

      1 - በመጸዳዳት ጊዜ ሀፍረተ ገላን

      (ዐውረትን) ከሰዎች እይታ መሰወርና መሸፈን፤ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹በጅኖች ዓይኖችና በኣደም ልጆች ሀፍረተ ገላ መካከል ያለው መጋረጃ ወደ መጸዳጃ ቦታ ሲገባ ‹ብስምል’ላህ› ማለት ነው፡፡ ›› [በትርምዚ የተዘገበ]ብለዋል፡፡

      2 - ልብስ ወይም ገላ በነጃሳ እንዳይነካ መጠንቀቅና ከነካ ማጠብ፤የአላህ መልእክተኛ ሁለት መቃብሮች አጠገብ ሲያልፉ ፡- ‹‹እየተሰቃዩ ነው፤የሚሰቃዩትም በትልቅ ነገር (ጥፋት) ምክንያት ሳይሆን ይኸኛው ራሱን ከሽንት አይጠብቅም፣አይጠነቀቅም ኖሯል፡፡›› [በአቡ ዳውድ የተዘገበ]ብለዋል፡፡

      3 - በውሃ ወይም በደረቅ ነገር መጸዳዳት (እስትንጃእ ወይም እስትጅማር)፤ከአነስ ብን ማሊክ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት የአላህ መልእክተኛ ﷺወደ መጸዳጃ ቦታ ሲሄዱ እኔና ሌላው ብላቴና (ልጅ) የውሃ መያዣውንና አንካሴ ይዘንላቸው እንሄድና በውሃ ይታጠቡ (እስትንጃእ ያደርጉ) ነበር፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ብሏል፡፡

      በመጸዳዳት ጊዜ የተከለከሉ (ሐራም የሆኑ) ነገሮች

      1 - ምድረበዳ ላይ በመጸዳዳት ጊዜ ፊትን ወደ ቅብላ ማዞር ወይም ጀርባን አለመስጠት፤ለመጸዳጃነት በተዘጋጀ የተለየ ግንባታ ከሆነ፣ ፊትን ወደ ቅብላ ማዞርንም ሆነ ለቅብላ ጀርባ መስጠትን መተው ተመራጭ ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹በመጸዳዳት ጊዜ በውሃ ሽንትም ሆነ በዓይነ ምድር ፊታችሁን ወደ ቅብላ አታዙሩ፡፡ ጀርባችሁንም አትስጡት፤ወደ ምሥራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]ብለዋል፡፡

      2 - በመንገዶች ላይ፣ሰዎች በሚጠለሉበት ጥላ ቦታና በመሰብሰቢያ ቦታዎች መጸዳዳት፤ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ሁለቱን መርገምት ተጠንቀቁ ሲሉ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሁለቱ መርገምት ምንድነው? ተብለው ሲጠየቁ በሰው መንገድ ወይም በሚያርፉበት ጥላ ቦታ የሚጸዳዳ ሰው ነው፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]ብለዋል፡፡

      3 - ወራጅ ባልሆነ እንደ ገላ መታጠቢያ ገንዳ ባለ ውሃ ውስጥ መረዳዳት፤ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹አንዳችሁ በማይፈስ የረጋ ውሃ [የረጋ ውሃ የማይወረድና የማይንቀሳቀስ ውሃ ነው] ላይ ይሸናና እዚያው ደግሞ ይታጠባልን? (አታድርጉ)፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]ብለዋል፡፡

      4 - የቁርኣን መጽሐፍ ይዞ መጸዳጃ ቤት መግባት ሐራም ነው፡፡

      በገላጣ ቦታ ላይ መጸዳዳት
      ሰው በሚጓዝበት መንገድ ላይ መጸዳዳት

      በመጸዳዳት ጊዜ የሚወደዱ (ሙስተሐብ) ነገሮች

      1 - ምድረበዳ ላይ በሚጸዳዱበት ጊዜ ከሰው እይታ ርቆ መሄድ፡፡

      2 - ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገባ ፡- ‹‹ብስምል’ላህ፣ አል’ሏሁም’መ እን’ኒ አዑዙ ብከ ምነልኹብሥ ወልኸባእሥ›› ትርጉሙ፡- ‹‹በአላህ ስም፣ አላህ ሆይ ከተባእትና አነስት ሰይጣናት (ተንኮል) በአንተ እጠበቃለሁ፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ማለት ነው፡፡

      3 - ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገባ የግራ እግርን ማስቀደም ሲወጣ ደግሞ ቀኑን ማስቀደም፡፡

      4 - በሚወጡበት ጊዜ ‹‹ጉፍራነከ›› [በአቡ ዳውድ የተዘገበ] (ምሕረትህን ስጠኝ) ማለት፡፡

      ሲወጡ ቀኝ እግርን ማስቀደም
      ሲገቡ ግራ እግርን ማስቀደም
      በረጋ ውሃ ላይ መሽናት
      በረጋ ውሃ ውስጥ መሽናት በደም መጣጭ ጥገኛ ትሎች የሚመጣውን የብልሃርዚያ በሽታ ያስከትላል፡፡

      በመጸዳዳት ጊዜ የተጠሉ (መክሩህ) ነገሮች

      1 - ሲጸዳዱ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ መናገር ወይም ሌሎችን ማናገር፤ይህም ከእብን ዑመር (ረዐ) በተላለፈውና ነቢዩ ﷺ በመጸዳዳት ላይ እያሉ በአቅራቢያቸው ያለፈ አንድ ሰው ሰላምታ ሲያቀርብላቸው ሰላምታውን አልመለሱለትም፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]በሚለው ሐዲሥ መሰረት ነው፡፡

      2 - ይሰረቅብኛል ወይም ይጠፋል የሚል ስጋት ከሌለ የአላህ U ስም ያለበትን ነገር ይዞ መግባት፡፡

      3 - ብልትን በቀኝ እጅ መንካት ወይም በቀኝ እጅ እስትንጃእም ሆነ እስትጅማር ማድረግ፤ ነቢዩ ﷺ ‹‹አንዳችሁ ሲሸና ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዝ፤ከዓይነ ምድር ሲጸዳዳም በቀኝ እጁ አያድርግ፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]

      4 - ተሳቢ እንስሳት እንዳይጎዱት ወይም እንዳይጎዳቸው ሲባል በስጥቆችና ጉድጓዶች መሽናት፡፡

      አላህን የሚያወሳ ነገር ያለበትን ነገር ይዞ መጸዳጃ ቤት መግባት
      እየተጸዳዱ መናገር
      በአውሬ ጉድጓድ ቦታዎች መሽናት
      የቁርኣን መጽሐፍ ይዞ መጸዳጃ ቤት መግባት
      ቆሞ መሽናት
      ነቢዩ ﷺ ቆሞ መሽናትን ከልክሏል፡፡ ይሁን እንጂ ሽንቱ የማይረጭበት መሆኑን ካረጋገጠ ይፈቀዳል፡፡ ከሑዘይፋ (ረዐ) ‹‹የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሰዎች ቆሻሻ በሚጥሉበት ስፍራ ሄደው ቆመው ተጸዳዱ፡፡›› [በቡኻሪና በሙስሊም የተዘገበ]የሚል ሐዲስ ተዘግቧል፡፡

      እስትንጃእና እስትጅማር

እስትንጃእ

ከሽንትና ዓይነ ምድር መውጫ ቅሪቱን በንጹሕ ውሃ ማስወገድ ነው፡፡

እስትጅማር

ከሽንትና ዓይነ ምድር መውጫ ቅሪቱን በድንጋይና መሰል ጠጣር ነገር ማስወገድ ነው፡፡

    እስትንጃእና እስትጅማርን የሚመለከት ድንጋጌ

    እስትንጃእ ማድረግ የተደነገገ ነው፡፡ ከአነስ ብን ማሊክ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት ‹‹የአላህ መልእክተኛ ﷺ ወደ መጸዳጃ ቦታ ይገቡና እኔና ሌላው ብላቴና (ልጅ) የውሃ መያዣውንና አንካሴ ይዘንላቸው ስንሄድ በውሃ ይታጠቡ (እስትንጃእ ያደርጉ) ነበር፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] የሚል ሐዲስ ተዘግቧል፡፡

    ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ በእስትጅማር ብቻ መወሰን ይፈቀዳል፡-

    1 - ሽንቱ ወይም ዓይነ ምድሩ ከተለመደ መውጫው አልፎ አለመዛመት፤አልፎ አካባቢውን ነክቶ ከሆነ ግን ውሃን መጠቀም የግድ ይላል፡፡

    2 - የፊትና የኋላ መውጫዎቹን ከነጃሳ ቅሪት ማጽዳት እንዲቻል፣በደረቅ ነገር ማጽዳቱ ሦስት ጊዜና ከዚያም በላይ መሆን፡፡

    ጠቃሚ ጉዳዮች

    -አየር ከሆድ በመውጣቱ ምክንያት እስትንጃእ አይደረግም፡፡

    -እስትንጃእ የበለጠ አጥሪና አጽጂ በመሆኑ ከእስትጅማር ይበልጥ ተመራጭ ነው፡፡

    እስትንጃእና እስትጅማር ያዘሉት ጥበብ

    1 - ከቆሻሻ መጽዳትና ነጃሳን ማስወገድ፡፡

    2 - ንጽሕናን መጠበቅና ለበሽታዎች መንስኤ ከሚሆኑ ነገሮች መራቅ፡፡

    ለእስትጅማር የሚዉሉ ነገሮች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

    ሀ- ንጹሕ (ጣህር) መሆን፣ነጃሳ በሆነ ነገር ማድረግ ትክክል አይደለም፡፡

    ለ- የተፈቀደ (ሐላል) በሆነገር መሆን፣በተከለከለ (ሐራም) በሆነ ነገር ማድረግ ትክክል አይደለም፡፡

    ሐ- አጥንት ወይም ፋንድያ አለመሆን፤ሰልማን አል ፋሪሲ (ረዐ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዓይነ ምድር ወይም በሽንት ጊዜ ፊታችንን ወደ ቅብላ እንዳናዞር፣በቀኝ እጅ እስትንጃእ እንዳናደርግ፣ከሦስት ባነሰ ድንጋይ እስትንጃእ (እስትጅማር) አንዳናደርግ፣በፋንድያ ወይም በአጥንት እስትንጃእ እንዳናደርግም ከልክለውናል፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]

    መ- ምግብና የተከበረ ነገር የተጻፈበት ወረቀትን የመሳሰለ ክብር የሚሰጠው ነገር አለመሆን፡፡

    በመጸዳጃ ቤት ወረቀት (ሶፍት) እስትጅማር ማድረግ
    በድንጋይ እስትጅማር ማድረግ
    በጨርቅ እስትጅማር ማድረግ
    በሚበላ ነገር እስትጅማር ማድረግ
    በአጥንት እስትጅማር ማድረግ
    የተከበረ ነገር ባለበት ወረቀት እስትጅማር ማድረግ
    በቀኝ እጅ እስትንጃእ ማድረግ
    በቀኝ አጅ እስትንጃእ ማድረግ የተፈቀደ (ጃእዝ) አይደለም፡፡ ነቢዩ ﷺ ‹‹አንዳችሁ በማይፈስ የረጋ ውሃ ላይ ይሸናና እዚያው ደግሞ ይታጠባልን? (አታድርጉ)፡፡›› [ሙስሊም የተዘገበ]ብለዋልና፡፡