ነጃሳዎችን የሚመለከቱ ብያኔዎች

7927

      የነጃሳ ትርጓሜ

የነጃሳ የቋንቋ ትርጉም

ቆሻሻ ማለት ነው፡፡

የነጃሳ ሸሪዓዊ ትርገም

በሸሪዓው እንዲወገድ የታዘዘ ቆሻሻ

    የነጃሳ ዓይነቶች

    1 - የሰው ሽንትና ዓይነ ምድሩ

    ይህም መስጊድ ውስጥ ለሸናው ገጠሬ ሰው (አዕራቢይ) ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹እነዚህ መስጊዶች ለሽንትም ሆነ ለቆሻሻ ነገር የተገቡ አይደሉም፤ለአላህ ውዳሴ (ለዝክር)፣ ለሶላትና ቁርኣንን ለመቅራት ብቻ (የተገቡ) ናቸው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]ባሉት መሰረት ነው፡፡

    2 - የወር አበባ ደም

    ኸውለህ ብንት የሳር ወደ ነቢዩ ﷺ መጥታ፡- ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ያለኝ አንድ ልብስ ብቻ ሲሆን የወር አበባዬ ይነከዋል›› ስትላቸው ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ከወር አበባሽ ስትጸጂ ደም የነካውን ቦታ እጥበሽ (በልብሱ) ስገጂበት፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ] አሏት፡፡

    ከወር አበባ ደም ውጭ ያለው የሚፈስ (መስፉሕ) [መስፉሕ ደም ቦታውን ለቆ የሚፈስ ደም ነው፡፡] ደምም ሆነ የማይፈስ ደም ንጹሕ (ጣህር) ነው፡፡ ይህም በሚከተለው ሐዲሥ መሰረት ነው፡- ‹‹ከጣዖታውያን ሙሽሪኮች አንዱ ከሙስሊሞች ሶላት በመስገድ ላይ የነበረውን አንድ ሰው በቀስት ወግቶት (ተወጊው) ፍላጻውን ነቅሎ ደሙ እየፈሰሰ መሰገዱን ቀጠለበት፡፡›› [በአቡ ዳውድ የተዘገበ]

    3 - ሥጋቸው የማይበላ እንስሳት ሽንትና ፋንድያ

    ማስረጃው ከእብን መስዑድ የተላለፈው የሚከተለው ሐዲሥ ነው፡ ‹‹ነቢዩ ﷺ ለመጸዳዳት ወጡና ሦስት ድንጋዮች እንዳመጣላቸው አዘዙኝ፤ ሁለት አግኝቼ ሦስተኛ ፈልጌ አጣሁና ፋንድያ ወስጄ አመጣሁላቸው፡፡ ሁለቱን ድንጋዮች ወሰዱና ፋንድያውን ጥለው ፡- ‹ይኸ ርክስ31 (የተነጀሰ) ነው፡፡› አሉ፡፡›› [በአቡ ዳውድ የተዘገበ]

    ሥጋቸው የሚበላ እንስሳት ሽንትና እበት ብያኔ (ሑክም) ምንድነው?
    ሥጋው የሚበላ እንስሳ ሽንትና እበቱ (በጠጡ) ጣህር (ንጹሕ) ነው፡፡ ከአነስ ብን ማሊክ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት የተወሰኑ ሰዎች መዲና መጥተው እዚያ ታመሙና የግመሎቹን ሽንትና ወተት ይጠጡ ዘንድ ሰዎቹን ነቢዩ ﷺ ወደ ዘካት (ሶደቃ) ግመሎች ላኳቸው፡፡ [በቡኻሪ የተዘገበ]

    4 - የበከቱ እንስሳት

    የበከተ እንስሳ ማለት ሸሪዓዊ በሆነ መንገድ ሳይታረደ የሞተ እንስሳ ነው፡፡ ይህን በማስመልከት አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- ወደኔ በተወረደው ውስጥ በክት፣ፈሳሽ ደም ወይም የአሳማ ስጋ፣እርሱ ርኩስ ነውና ወይም በአመጥ ከአላህ ስም ሌላ በርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፤. . . ›› [አል-አንዓም፡145]

    ፡፡ አንድ እንስሳ ሳይታረድ በሕይወት እያለ የተቆረጠ የእንስሳ አካልም በበክት ውስጥ ይጠቃለላል፡፡

    የበከተ እንስሳ

    የሚከተሉት ግን በዚህ ውስጥ አይካተቱም፡-

    1 - የሞተ ዓሳና አንበጣ ፡-

    ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሁለት (ዓይነት) የሞቱ እንስሳትና ሁለት (ዓይነት) ደሞች የተፈቀዱ (ሐላል) ተደርገውልናል፡፡ ሳይታረዱ ሞተው የተፈቀዱት ዓሳና አንበጣ ሲሆኑ ሁለቱ ደሞች ደግሞ ጉበትና ጣፊያ ናቸው፡፡›› [በአሕመድ የተዘገበ]

    ዓሳ
    አንበጣ

    2 - እንደ ዝንብ ያሉ ፈሳሽ ደም የሌላቸው የሞቱ ነፍሳት ፡-

    ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ዝንብ በአንዳችሁ ዕቃ ውስጥ ሲገባበት ሙሉ በሙሉ ዝንቡን ያጥልቅበትና አውጥተው ይጣለው፤በአንድ ክንፉ ፈውስ በልላ ክንፉ በሽታ አለበትና፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ]

    ዝንብ

    5 - የአሳማ ሥጋ

    ይህን በማስመልከት አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- ወደኔ በተወረደው ውስጥ በክት፣ፈሳሽ ደም ወይም የአሳማ ስጋ፣እርሱ ርኩስ ነውና ወይም በአመጥ ከአላህ ስም ሌላ በርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፤. . . ››[አል-አንዓም፡145]፡፡

    አሳማ

    6 - የውሻ ልጋግ

    ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ያንዳችሁን ዕቃ ውሻ በአፉ (ምላሱን በማስገባት) ከለከፈው የሚጸዳው (ዕቃውን) ሰባት ጊዜ አንደኛውን ዙር በአፈር በማጠብ ነው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]

    የውሻ መልከፍ ማለት ቢጠጣም ባይጠጣም በዕቃዎች ውስጥ ምላሱን አስገብቶ የመነካካቱ ሁኔታ ነው፡፡

    የውሻ ልጋግ (በምላሱ መልከፍ)

    7 - መዚይ

    መዚይ ስለ ሩካቤ ሥጋ በማሰብ ወይም ከተቃራኒ ጾታ ጋር በመነካካትና በመተሸሻት ምክንያት ከብልት የሚወጣ ነጣ ያለና የመጣበቅ ባህሪ ያለው ፈሳሽ ነው፡ ሲወጣ የእርካታ ስሜት የማፈጥርና የማይደፍቅ ሲሆን ከወጣ በኋላም የመለዘብ ስሜት አያሳድርም፡ ምናልባትም ሲወጣ ለሰውየው ምንም ላይሰማው ይችላል፡፡

    ነቢዩ ﷺ ዐሊይ ብን አቡ ጧሊብ (ረዐ) ስለ መዚይ ሲጠይቋቸው እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ዉዱእ አድርግ፤ብልትህንም ታጠብ፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]

    8 - ወዲይ

    ወዲይ ከውሃ ሽንት በኋላ ከብልት የሚወጣ ወፈር ያለ ነጭ ፈሳሽ ነው፡፡

    መኒይ ንጹሕ (ጣህር) መሆኑ

    መኒይ (ወንዴ የዘር ፈሳሽ) ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ ከብልት የሚደፈቅና ከወጣ በኋላ የመሟሸሽ ሁኔታ የሚከተለው ነጭ ወፍራም ፈሳሽ ነው፡፡ የተምር እሸት ጠረን ያለው ሲሆን ከስንዴ ሊጥ ጠረን የቀረበ ነው፡፡

    መኒይ ጣህር ነው፤ነጃሳ ቢሆን ኖሮ ነቢዩ ﷺ እንዲታጠብ ባዘዙ ነበር፡፡

    መኒይ እርጥብ ከሆነ በውሃ ማጠብ ደርቆ ከሆነ ደግሞ በመፈግፈግ ማስወገድ በቂ ነው፡፡ ከዓእሻ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት ‹‹የአላህ መልእክተኛ ﷺ መኒይ የነካውን ልብስ አጥበው የታጠበውን ቦታ (እርጥበቱን ) በዓይኔ እያየሁ በዚያው ልብስ ለሶላት ይሄዱ ነበር፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]

    ብለዋል፡፡ በሙስሊም ዘገባ ደግሞ ‹‹ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ልብስ ላይ በሚገባ ፈግፍጌ በዚያው ይሰግዱ ነበር፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]የሚል ተመልክቷል፡፡

    እርጥብ ከሆነ ማጠብ
    ደረቅ ከሆነ መፈግፈግ
    አልኮል
    አልኮል ሕሊናዊ እርኩስነቱና ነጃሳነቱ፣ መጠጣቱ ደግሞ ከከባዳ ኃጢአቶች አንዱ መሆኑ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ቁሳዊ ነጃሳነት የሌለው ጣህር ነው፡፡ ‹‹እላንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፣ቁማርም፣ጣዖታትም፣አዝላምም (የመጠንቆያ እንጨቶች) ከሰይጣን ሥራ የሆኑ እርኩሶች ብቻ ናቸው፤(እርኩስን) ራቁት፤ልትድኑ ይከጀላልና፡፡›› [አል-ማኢዳህ፡145]
    ፡፡ በሚለው የአላህ ቃል ውስጥ የተመለከተው ርክሰት ቁማርና ጣዖታትንም (መይስር እና አንሷብ) የሚያካትተው ሕሊናዊ ርክሰት እንጂ አካላዊና ቁሳዊ ነጃሳነት አይደለም፡፡
    አስካሪ መጠጦች

    ነጃሳዎችን የማስወገጃ መንገዶች

    1 - መሬትን ከነጃሳ የሚጸዱበት መንድ

    መሬት ነጃሳ ከነካው በውሃም ይሁን ወይም በሌላ ነገር ነጃሳው ይወገዳል፡፡ መስጊድ ውስጥ የሸናውን ገጠሬ ዐረብ አስመልክተው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋልና፡ ‹‹ተውት (ሰውየውን አትንኩት)፤ በሸናበት ቦታ ላይ

    ባልዲ ሙሉ ወይም በትልቅ ባልዲ ውሃ ድፉበት ፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]

    መሬቱን የበከለው ፈሳሽ ነጃሳ ከሆነ በመድረቁ ብቻ መሬቱ የጸዳ ይሆናል፡፡ ይህም ከአቡ ቀላባ በተላለፈውና ፡- ‹‹መሬት ከደረቀ ጣህር ሆኗል፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ]

    የውሃን መጠን በመጨመር ማጽዳት
    ፈሳሽ ነጃሳ መሬት ላይ
    የፈሳሽ ነጃሳ መድረቅ

    2 - የተነጀሰ ውሃ የሚጸዱበት መንገድ

    ነጃሳ የገባበት ውሃ ቅሪቱ እንዲወገድ የበዛ ውሃ በመጨመር ይጸዳል፡፡ በዘመናዊ የማጥሪያ ዘዴዎችም ሊጠራ ይችላል፡፡

    በዘመናዊ ዘዴዎች ማጽዳት
    የውሃን መጠን በመጨመር ማጽዳት

    3 - የተነጀሰ ልብስ የሚጸዱበት መንገድ

    ነጃሳው እስኪወገድ ድረስ በውሃ ፈግፍጎ በማጠብና በመጭመቅ ይጸዳል፡፡

    የተነጀሰ ልብስ የሚጸዱበት መንገድ

    4 - ምንጣፍ ከነጃሳ የሚጸዱበት መንገድ

    ነጃሳው እስኪወገድ ድረስ በውሃ ይታጠባል፤፤ወይም በዘመናዊ ማጽጃዎች በመፈግፈግም ይጸዳል፡፡

    ምንጣፍ የሚጸዱበት መንገድ

    5 - የሞተ እንሳሳ የሚጸዱበት መንገድ

    1 - ሥጋው የሚበላ እንስሳ ቆዳ ፡-

    ይህ ቆዳውን ከውስጥና ከውጭ በኩል በማልፋት ከነጃሳ ይጸዳል፡፡ ይህም በሚከተለው የነቢዩ ﷺ ሐዲስ መሰረት ነው፡- ‹‹ቆዳ ከተለፋ ንጹሕ (ጣህር) ሆኗል፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]

    ቆዳ መልፋት ማለት ቆዳው ለስልሶ መጥፎ ጠረኑ እስኪወገድ ድረስ የተወሰኑ ኬሚካሎችን በመጠቀም ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡

    ሥጋው የሚበላ እንስሳ በሸሪዓዊ መንገድ ታርዶ ከሞተ ግን ቆዳው ጣህር ነው፡፡

    ቆዳን ማልፋት
    ሥጋው የሚበላ እንስሳ

    2 - የበከተ ሥጋው የማይበላ እንስሳ ቆዳ፡

    በሕይወት እያለ በቁሙ ጣህር ቢሆን እንኳ ፣በሸሪዓዊ መንገድ መታረዱ ሐላል የማይሆነው እንስሳ ቆዳ ቢለፋም ንጹሕ (ጣህር) አይሆንም፡፡

    ሥጋው የማይበላ እንስሳ

    6 - ምግብ መብላት ያልጀመረ ወንድ ወይም ሴት ሕጻን ሽንት የሚጸዱበት መንገድ

    የሴት ሕጻን ሽንት ይታጠባል፡፡ የወንድ ሕጻን ሽንት ግን ላዩ ላይ ውሃ ማፍሰስ ብቻ በቂ ይሆናል፡፡ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋልና ፡- ‹‹የሴት ሕጻን ሽንት ይታጠባል፤የወንድ ሕጻን ሽንት ውሃ ይረጭበታል፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ]

    የወንድ ሕጻን ሽንትን ውሃ ላዩ ላይ መርጨት
    የሴት ሕጻን ሽንትን ማጠብ

    7 - ውሻ የለከፈው ነገር የሚጸዱበት መንገድ

    ውሻ በአፉና በምላሱ የነካውን ነገር ሰባት ጊዚ አንደኛውን በአፈር በማጠብ ይጸዳል፡፡ ነቢዩ ﷺእንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ያንዳችሁን ዕቃ ውሻ በአፉ (ምላሱን በማስገባት) ከለከፈው የሚጸዳው (ዕቃውን) ሰባት ጊዜ አንደኛውን ዙር በአፈር በማጠብ ነው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]

    በአፈር ማጽዳት አንድ ጊዜ ከዚያም በእጥበት ማጽዳት 6 ጊዜ

    8 - መዚይና ወዲይ የሚጸዱበት መንገድ

    ብልትን በማጠብና ዉዱእ በማድረግ፡ ነቢዩ ﷺ ዐሊይ ብን አቡ ጧሊብ (ረዐ) ስለ መዚይ ሲጠይቋቸው እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ዉዱእ አድርግ፤ብልትህንም ታጠብ፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]

    መዚይ ወይም ወዲይ የነካውን ልብስ በተመለከተ በነኩት ቦታ ላይ ውሃ በመርጨት ይጸዳል፡ ሰህል ብን ሐኒፍ ባስተላለፉት ሐዲስ፡- ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ልብሴን የነካውን እንዴት አደርጋለሁ ስላቸው እፍኝ ውሃ ወስደህ ነክቶት ባየህበት የልብሱ ቦታ ላይ መርጨት ብቻ በቂህ ነው አሉኝ፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበበ] ብለዋል፡፡

    9 - የወር አበባ ደም የሚጸዱበት መንገድ

    በውሃ በማጠብ ይጸዳል፡፡ የቅሪቱ መኖር ችግር አይኖረውም፤ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ውሃ ይበቃሻል፤የቅሪቱ መኖር ችግር የለውም፡፡›› [አቡ ዳዉድ የተዘገበ] ብለዋልና፡፡

    10 - ጫማ የሚጸዱበት መንገድ

    የነጃሳው ቅሪት እስኪወገድ ድረስ መሬት ላይ በመፈግፈግ ይጸዳል፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹አንዳችሁ በጫማው አዋኪ ነገር ከረገጠ አፈር (የነጃሳ) መጽጃው ነው፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ] ብለዋል፡፡

    ጫማን መሬት ላይ በመጥረግ ማጽዳት

    11 - የሴት ረዥም ልብስ የሚጸዱበት መንገድ

    ረዥም የሴት ቀሚስ በጫፉ ላይ ነጃሳ ቢጣበቅበት ንጹሕ በሆነው ቦታ መሄዷ ይበቃታል፤መሬቱ ራሱ ያጸዳዋልና፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ከኋላው ያለው ያጸዳዋል፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ] ብለዋል፡፡

    መሬት የሴትን ልብስ ያጸዳል

    12 - ጠጣር ምግቦች የሚጸዱበት መንገድ

    ነጃሳው ያለበትንና በዙሪያው ያለውን በማስወገድ ይጸዳል፡፡ ቀሪው በመሰረታዊ ንጽሕናው ላይ እንዳለ ይቀራል፡፡ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ፡- ‹‹ቅቤ ውስጥ ስለ ወደቀች አይጥ ተጠይቀው ‹‹አስወጧትና በዙሪያዋ ያለውን አስወግዳችሁ ቅቤያችሁን ተመገቡ፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ]ብለዋል፡፡

    አይጥ ገብቶ የሞተበት ቅቤ

    13 - እንደ መስተዋትና ብርጭቆ ያሉ የጠሩ ገጾች የሚጸዱበት መንገድ

    የነጃሳው ቅሪት እስኪወገድ ድረስ ይወለወላል፡፡

    መስተዋት በመወልወል ይጸዳል
    ነጃሳዎችን የሚመለከቱ ጠቃሚ ነጥቦች

    1 - ነጃሳ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነገር እስካልቀረበ ድረስ ነገሮች ሁሉ በመሰረቱ ንጹሕ (ጣህር) ናቸው፡፡

    2 - በአንድ ነገር ላይ ነጃሳ ከወደቀና የነካው ቦታ ተለይቶ ያልታወቀ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ይታጠባል፡፡

    3 - ነጃሳ በሆነ ነገር ውስጥ ሟምቶ ከተዋሐደው - ለምሳሌ ያህል የአህያ ፋንድያ ተቃጥሎ ወደ አመድነት ቢለወጥ - በዚሁ ይጸዳል፡፡

    ፋንድያ ወደ አመድነት ሲለወጥ የጸዳ ያደርገዋል


Tags: