ሱነኑል ፍጥረህ አላህ U የሰውን ልጅ በጥሩ አኳኋኑና በውብ ተክለሰውነቱ ምሉእ ይሆን ዘንድ ከጥንቱ ከመሰረቱ ካኖረበት ተፈጥሮ ጋር የተያያዙ ነገሮች ናቸው፡፡
ሱነኑል ፍጥረህ አላህ U የሰውን ልጅ በጥሩ አኳኋኑና በውብ ተክለሰውነቱ ምሉእ ይሆን ዘንድ ከጥንቱ ከመሰረቱ ካኖረበት ተፈጥሮ ጋር የተያያዙ ነገሮች ናቸው፡፡
ከዓእሻ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት የአላህ መልእክተኛﷺ ‹‹አስር ነገሮች የተፈጥሮ ደንቦች ናቸው (እነሱም) ፡- ሪዝን ማሳጠር፣ጺምን ማሳደግ፣ጥርስን መፋቅ፣ውሃ በመሳብ አፍንጫን ማጽዳት፣ጥፍር መቆረጥ፣የጣት ጀርባ እጥፋቶችን ማጠብ፣የብቢት ጠጉርን መንጨት፣ጭገርን መላጨት፣ ብልትን በውሃ ማጠብና መጉመጥመጥ ናቸው፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]
ከአራክ ዛፍ እንጨትና ከመሳሰለው ተወስዶ መጥፎ ጠረንና የምግብ ቅሪትን ከአፍ ለማስወገድ ጥርስን ለማጽዳት የሚያገለግል ነው፡፡
ስዋክን መጠቀም በሁሉም ወቅቶች ሱንና ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ሰዋክ አፍን የሚያጸዳ ጌታንም የሚያስደስት ነው፡፡›› [በአሕመድ የተዘገበ] ብለዋል፡፡
ቀጥሎ በተመለከቱት ቦታዎች ላይ ግን ሰዋክን መጠቀም በጣም የጠበቀ ሱንና ነው፡-
ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ ኡመቴ (ሕዝቤ) ላይ ማጥበቅ ባይሆንብኝ ኖሮ በያንዳንዱ ዉዱእ ወቅት ሰዋክን እነዲጠቀሙ (ጥርሳቸውን እንዲፍቁ) ባዘዝኳቸው ነበር፡፡›› [በአሕመድ የተዘገበ] ብለዋልና፡፡
ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ኡመቴ (ሕዝቤ) ላይ ማጥበቅ ባይሆንብኝ ኖሮ በያንዳንዱ ሶላት ወቅት ስዋክን እንዲጠቀሙ (ጥርሳቸውን እንዲፍቁ) ባዘዝኳቸው ነበር፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ብለዋልና፡፡
ምቅዳድ (ረዐ) አባታቸውን በመጥቀስ ባስተላለፉት መሰረት ፡- ‹‹ነቢዩ ﷺ ወደ ቤታቸው በሚገቡበት ጊዜ አስቀድመው ምን ያደርጉ እንደ ነበር ዓእሻን (ረዐ) ጠይቄ፣በሰዋክ ነው አሉኝ፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ] ብለዋል፡፡
ከሑዘይፋ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት፡- ‹‹ነቢዩ ﷺ ሌሊት ሲነሱ አፋቸውን በሰዋክ ያጸዱ ነበር፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] ብለዋል፡፡
ዐሊይ (ረዐ) በሰዋክ አዘው ነቢዩﷺ ፡- ‹‹አንድ የአላህ አገልጋይ ጥርሱን ፍቆ (ሰዋክ ተጠቅሞ) ተነስቶ ከሰገደ፣መልኣክ ከጀርባው ቆሞ ቅራኣውን በማዳመጥ - ወይም ይህን በመሰለ አባባል - አፉን በአፉ ላይ እስከማድረግ ድረስ ወደርሱ ይቀርባል፤ከአፉ የሚወጣው ቁርኣን ወደ መልኣኩ ሆድ ውስጥ የሚገባ ይሆናልና አፋችሁን ለቁርኣን አጽዱ፡፡›› [በአል በዝዛር የተዘገበ] ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ውሃን ወደ አፍ አስገብቶ ማንቀሳቀስ
ወሃን ወደ አፍንጫ በመሳብ ማስገባት
የሽንትን ወይም የዓይነ ምድርን ቅሪት ከመውጫው ቦታ ላይ ማስወገድ
ማለት የተፈለገው ለውበት፣ለንጽሕናና ከካፍሮች ለመለየት ሲባል ከስር ማሳጠር ነው፡፡
ማሳደግ ማለት ባለበት መተውና አለመንካት ማለት ነው፡፡
ብልት አካባቢ የሚበቅለውን ጸጉር መላጨት
የወንድ ብልት ጫፍ የሚሸፍነውን ቆዳ ማስወገድ ነው፡፡
ከወንድ ብልት ማስገቢያ ቦታ በላይ ያለውን ትርፍ ሥጋ መቁረጥ ነው፡፡
የወንድ ገርዛት ‹ኽታን› ሲባል የሴት ደግሞ ‹ኽፋድ› (ማሳጥር) ይባላል፡፡ ነቢዩﷺ ለኡምሙ ዐጥያ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አሳጥሪ ግን ከስር አታንሺው፤ለፊት የበለጠ ውበት የሚሰጥ ሲሆን ባሏ ዘንድም የበለጠ ተወዳጅ ነውና፡፡›› [በአልሓክም የተዘገበ]
ግርዛት ለወንድ ግዴታ ሲሆን ለሴት ግን ሱንና ነው፡፡
የወንድ ግርዛት ያዘለው ጥበብ የብልቱን ራስ በሚሸፍነው ቆዳ ውስጥ ያለውን ነጃሳ ማጽዳቱ ሲሆን፣የሴት ግርዛት ደግሞ የፊቷን ውበት መጨመሩ ነው፡፡
እንዳይረዝም አድርጎ ጫፎቹን መቁረጥ ነው፡፡
ማስወገዱ ለንጽሕና አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑና በጸጉሩ ምክንያት የሚፈጠረውን መጥፎ ጠረን ለማጥፋት ሲባል ማስወገድ ነው፡፡
በራጅም- ከመዳፎች ጀርባ (አይበሉባ) በኩል ያሉ የጣቶች መገጣጠሚያዎች፡፡
አንዳንድ ሊቃውንት (ዑለማእ) በጆሮዎች ውስጥ፣በአንገት አካባቢና በተለያ የአካል ክፍሎች የሚጠራቀሙ ቆሻሻዎችንም ከዚሁ ጋር አካትተዋል፡፡