በሁለት ነገሮች መካከል መለየት ማለት ነው፡፡
በሁለት ነገሮች መካከል መለየት ማለት ነው፡፡
የሸሪዓው ባለቤት ለዕባዳ ለይቶ የወሰነው ጊዜና ቦታ ነው፡፡
የሸሪዓው ባለቤት ለሐጅና ለዑምራ እሕራም ማድረጊያ አድርጎ የደነገጋቸው ቦታዎች ናቸው፡፡
ሐጅ ወይም ዑምራ ለማድረግ የፈለገ ሰው እሕራም ሳያደርግ ሚቃቱን ማለፍ አይፈቀድም፡፡ እነሱም አምስት ሚቃቶች ናቸው [ሚቃቶች ስፋታቸው ርዝመታቸውና ጥልቀታቸው፣ሸይክ ዐብደላህ አልበሳም፣የእስላማዊ ፍቅህ አካዳሚ መጽሔት ቁ 3 ክ 3 ገጽ 1553]፡-
በአሁኑ ጊዜ ከመዲና በስተደቡብ አቅጣጫ ይገኛል፡፡ አብያር ዐሊ ተብሎም የሚጠራ ሲሆን ከመካ 420 ኪሜ ያህል ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ዙልሑሌፋ የመዲና ሰዎች ሚቃት ነው፡፡
ጁሕፋ ራቢግ ከተማ አቅራቢያ ከመካ 186 ኪሜ ያህል ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ጁሕፋ የሻም የግብጽና የሞሮኮ ሰዎች ሚቃት ነው፡፡
የለምለም የየመን ሰዎች ወደ መካ በሚጓዙበት መንገድ ላይ የሚገኝና ዛሬ ሰዕዲያ ተብሎ የሚጠራ ትልቅ ሸለቆ ሲሆን፣ከመካ በ120 ኪሜ ያህል ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
የለምለም የየመን ሰዎች ሚቃት ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ሰይል አልከቢር ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ከመካ 75 ኪሜ ያህል ይርቃል፡፡
ቀርኑል መናዝል የነጅድና የጧእፍ ሰዎች ሚቃት ነው፡፡ ከርሱ በላይ በጧእፍ መንገድ ላይ ከሀዳ አቅጣጫ በኩል ዋዲ መሕረም ተብሎ የሚጠራ ቦታ የሚገኝ ሲሆን ሁለቱም የነጅድና በጧእፍ መንገድ በኩል የሚመጡ ሰዎች ሚቃት ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ደሪባ ወይም ኹረይባት ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ ከመካ በስተምሥራቅ በ100 ኪሜ ያህል ርቀት ላይ የሚገኝና ዛሬ ሰው የማይኖርበት ቦታ ነው፡፡
ዛቱ ዕርቅ ከምሠራቅ በኩል የሚመጡ የዒራቅ የኢራንና ከነሱ ወዲያ የሚመጡ ሰዎች ሚቃት ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ማስረጃው እብን ዐባስ (ረዐ) ባስተላለፉት መሰረት የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለመዲና ሰዎች ዙልሑለይፋን፣ለሻም ሰዎች ጁሕፋን፣ለነጅድ ሰዎች ቀርኑል መናዝልን፣ለየመን ሰዎች የለምለምን ሚቃት አድርገው ፡- ‹‹እነዚህ ለነሱና የነዚያ ነዋሪዎች ሳይሆኑ በነሱ በኩል ሐጅና ዑምራ ፈልገው ለሚመጡትም ናቸው፡፡ ከነዚህ ወዲህ ያሉት (ሚቃታቸው) ከሚነሱበት ቦታ ሲሆን የመካ ሰዎች እንኳ ከመካ ነው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ]አሉ ብለዋል፡፡
ዛቱ ዕርቅ ግን በዚህ ሐዲስ ውስጥ ያልተጠቀሰ ሲሆን ሚቃት ያደረጉት ዑመር ብን አልኸጧብ (ረዐ) ናቸው፡፡ [በቡኻሪ የተዘገበ]
- እነዚህን ሚቃቶች እሕራም ሳያደርግ ያቋረጠ ሰው ከቻለ መመለስ ይኖርበታል፡፡ መመለስ ካልቻለ ግን ቤዛ (ፍድያ) መክፈል ሲኖርበት፣እሱም መካ ውስጥ አርዶ ሥጋውን ለሐረም ሚስኪኖች የሚከፋፍለው አንድ ፍየል ነው፡፡
- የነዚህ ሚቃቶች ሰዎች ሳይሆን በነሱ በኩል የሚያልፍ ሰው ከነዚሁ ሚቃቶች እሕራም ያደርጋል፡፡ ከነጅድ ነዋሪዎች የሆነ አንድ ሰው በመዲና መንገድ ቢመጣ ከአብያር ዐሊ እሕራም ያደርጋል፡፡
- መኖሪያው በመካ አቅጣጫ ከሚቃቶቹ ወዲህ እንደ ጅዳ በሕራና ሸራእዕ የሆነ ሰው ለሐጅና ዑምራ እሕራም የሚያደርገው ካለበት ቦታ ነው፡፡
- በየብስ በባሕርም ሆነ በአየር በሚቃቶች በኩል በማያልፍ መንገድ የመጣ ሰው፣ይበልጥ ከሚቀርቡት ሚቃቶች ትይዩ ሲደርስ እሕራም ያደርጋል፡፡ ዑመር (ረዐ) ፡ ‹‹ከመንገዳችሁ በኩል የርሱ (የሚቃቱ) ትይዩ የት እንደሆነ አስተውሉ፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] ብለዋልና፡፡
- የመካ ነዋሪ ወይም ነዋሪ ያልሆነና መካ ውስጥ ሆኖ ለሐጅ ንይያ ያደረገ ሰው፣ከዚያው ካለበት እሕራም ያደርጋል፡፡ ዑምራን በተመለከተ ግን ቅርቡ ወደ ሆነ እንደ ተንዒምና ጀዕራና ወደ መሳሰሉ ከሐረም ክልል ውጭ ወዳሉት ቦታዎች በመሄድ እሕራም ያደርጋል፡፡
የሐጅና ዑምራ ጊዜ
የሐጅ የጊዜ ሚቃት የሐጅ ወራት ሲሆኑ እነሱም ሸዋል፣ዙልቀዕዳና ከዙልሕጃ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ናቸው፡፡
ዓመቱ በሙሉ የዑምራ የጊዜ ሚቃት ነው፡፡