ሱነኑል ፍጥረህ (የተፈጥሮ ደንቦች)
ሱነኑል ፍጥረህ አላህ U የሰውን ልጅ በጥሩ አኳኋኑና በውብ ተክለሰውነቱ ምሉእ ይሆን ዘንድ ከጥንቱ ከመሰረቱ ካኖረበት ተፈጥሮ ጋር የተያያዙ ነገሮች ናቸው፡፡
መፋቂያ
ከአራክ ዛፍ እንጨትና ከመሳሰለው ተወስዶ መጥፎ ጠረንና የምግብ ቅሪትን ከአፍ ለማስወገድ ጥርስን ለማጽዳት የሚያገለግል ነው፡፡
ስዋክን መጠቀም በሁሉም ወቅቶች ሱንና ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ሰዋክ አፍን የሚያጸዳ ጌታንም የሚያስደስት ነው፡፡›› [በአሕመድ የተዘገበ] ብለዋል፡፡
ቀጥሎ በተመለከቱት ቦታዎች ላይ ግን ሰዋክን መጠቀም በጣም የጠበቀ ሱንና ነው፡-
1 - በዉዱእ ጊዜ
ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ ኡመቴ (ሕዝቤ) ላይ ማጥበቅ ባይሆንብኝ ኖሮ በያንዳንዱ ዉዱእ ወቅት ሰዋክን እነዲጠቀሙ (ጥርሳቸውን እንዲፍቁ) ባዘዝኳቸው ነበር፡፡›› [በአሕመድ የተዘገበ] ብለዋልና፡፡
2 - በሶላት ጊዜ
ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ኡመቴ (ሕዝቤ) ላይ ማጥበቅ ባይሆንብኝ ኖሮ በያንዳንዱ ሶላት ወቅት ስዋክን እንዲጠቀሙ (ጥርሳቸውን እንዲፍቁ) ባዘዝኳቸው ነበር፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ብለዋልና፡፡
3 - ወደ ቤት በሚገባበት
ምቅዳድ (ረዐ) አባታቸውን በመጥቀስ ባስተላለፉት መሰረት ፡- ‹‹ነቢዩ ﷺ ወደ ቤታቸው በሚገቡበት ጊዜ አስቀድመው ምን ያደርጉ እንደ ነበር ዓእሻን (ረዐ) ጠይቄ፣በሰዋክ ነው አሉኝ፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ] ብለዋል፡፡
4 - ከእንቅልፍ ሲነቃ ፡-
ከሑዘይፋ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት፡- ‹‹ነቢዩ ﷺ ሌሊት ሲነሱ አፋቸውን በሰዋክ ያጸዱ ነበር፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] ብለዋል፡፡
5 - ቁርኣን በሚቀራበት ጊዜ ፡-
ዐሊይ (ረዐ) በሰዋክ አዘው ነቢዩﷺ ፡- ‹‹አንድ የአላህ አገልጋይ ጥርሱን ፍቆ (ሰዋክ ተጠቅሞ) ተነስቶ ከሰገደ፣መልኣክ ከጀርባው ቆሞ ቅራኣውን በማዳመጥ - ወይም ይህን በመሰለ አባባል - አፉን በአፉ ላይ እስከማድረግ ድረስ ወደርሱ ይቀርባል፤ከአፉ የሚወጣው ቁርኣን ወደ መልኣኩ ሆድ ውስጥ የሚገባ ይሆናልና አፋችሁን ለቁርኣን አጽዱ፡፡›› [በአል በዝዛር የተዘገበ] ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የሰዋክ ጥቅሞች
ከሰዋክ ጥቅሞች መካከል፡- በዱንያ ላይ አፍን ያጸዳል፣በወዲያኛው ሕይወት በኣኽራ ደግሞ የአላህን ውዴታ ያስገኛል፤ጥርስን ያጠነክራል፤ድድን ያጠብቃል፤ድምጽን ያጠራል፤ሰውን ያነቃቃል፡፡
መፋቂያ
2 - መጉመጥመጥና ውሃ በመሳብ አፍንጫን ማጥራት
መጉመጥመጥ
ውሃን ወደ አፍ አስገብቶ ማንቀሳቀስ
እስትንሻቅ
ወሃን ወደ አፍንጫ በመሳብ ማስገባት
አፍን መጉመጥመጥ
በአፍንጫ ውሃ ስቦ ማስወጣት
3 - እስትንጃእ
እስትንጃእ
የሽንትን ወይም የዓይነ ምድርን ቅሪት ከመውጫው ቦታ ላይ ማስወገድ
ብልት አካባቢ የሚበቅለውን ጸጉር መላጨት (እስትሕዳድ)
ብልት አካባቢ የሚበቅለውን ጸጉር መላጨት
የወንድ ግርዛት (ኽታን)
የወንድ ብልት ጫፍ የሚሸፍነውን ቆዳ ማስወገድ ነው፡፡
የሴት ግርዛት (ኽፋድ)
ከወንድ ብልት ማስገቢያ ቦታ በላይ ያለውን ትርፍ ሥጋ መቁረጥ ነው፡፡
የወንድ ገርዛት ‹ኽታን› ሲባል የሴት ደግሞ ‹ኽፋድ› (ማሳጥር) ይባላል፡፡ ነቢዩﷺ ለኡምሙ ዐጥያ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አሳጥሪ ግን ከስር አታንሺው፤ለፊት የበለጠ ውበት የሚሰጥ ሲሆን ባሏ ዘንድም የበለጠ ተወዳጅ ነውና፡፡›› [በአልሓክም የተዘገበ]
ግርዛት ለወንድ ግዴታ ሲሆን ለሴት ግን ሱንና ነው፡፡
የወንድ ግርዛት ያዘለው ጥበብ የብልቱን ራስ በሚሸፍነው ቆዳ ውስጥ ያለውን ነጃሳ ማጽዳቱ ሲሆን፣የሴት ግርዛት ደግሞ የፊቷን ውበት መጨመሩ ነው፡፡
8- ጥፍርን መቆረጥ
እንዳይረዝም አድርጎ ጫፎቹን መቁረጥ ነው፡፡
ጥፍሮችን መቆረጥ
9 - የብቢትን ጸጉር መንጨት
ማስወገዱ ለንጽሕና አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑና በጸጉሩ ምክንያት የሚፈጠረውን መጥፎ ጠረን ለማጥፋት ሲባል ማስወገድ ነው፡፡
ብቢትን መንጨት
10 - ከመዳፍ ጀርባ የሚገኙ የጣት መገጣጠሚያዎችን (በራጅም) መታጠብ
ከመዳፍ ጀርባ የሚገኙ የጣት መገጣጠሚያዎች
በራጅም- ከመዳፎች ጀርባ (አይበሉባ) በኩል ያሉ የጣቶች መገጣጠሚያዎች፡፡
አንዳንድ ሊቃውንት (ዑለማእ) በጆሮዎች ውስጥ፣በአንገት አካባቢና በተለያ የአካል ክፍሎች የሚጠራቀሙ ቆሻሻዎችንም ከዚሁ ጋር አካትተዋል፡፡
በውጭ መዳፍ በኩል ያሉ የጣት መገጣጠሚያዎች
አርባ ቀናት
ጥፍሮች፣የብብት ጸጉር፣የብልት አካባቢ ጸጉርና ሪዝም ከአርባ ቀናት በላይ ባሉበት መቆየታቸው የተጠላ (መክሩህ) ነው፡፡ አነስ ብን ማሊክ (ረዐ) ፡- ‹‹የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሪዝ ማሳጠርን፣ጥፍር መቆረጥን፣ጭገር መላጨትንና የብቢት ጸጉር መንጨትን በተመለከተ ከአርባ ቀን በላይ እንዳንተዋቸው ጊዜ ወስነውልናል፡፡›› [በትርምዚ የተዘገበ]